Sun Computer Training institute !

Sun Computer Training Institute 

/ሰን የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ተቋም /

 Organization

SUN Computer   Training Institute is a collaboration Professionals. We the members have different and Best experience about Cisco system, Microsoft, Linux and A+, Server Installation and configuration and etc with Experience in the fields. But more than everything, we have a great   inspiration and interest to give efficient service in the ICT field and to contribute our part to the growing ICT industry in our country.

"  More than everything, we have a great   inspiration and interest to give efficient service in the ICT field."

ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት ወደ “ግሉባላይዜሽን” እየገሠሠች ባለችበት ሂደት ዉስጥ መረጃ ከፍተኛዉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል ፡፡ ከመቼዉም ጊዜ ይልቅ መረጃ በግልም ሆነ በህብረተሰብ ደረጃ ፈጣን የዕድገት መሰላል እና ህብረተሰብን ከህብረተሠብ ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ሆኗል፡፡ በዚህ ዘመን መረጃን ቀድሞ ማግኘት የኢኮኖሚ፣ የለዉጥና የእድገት ቁልፍ ነዉ፡፡

የመረጃ ቴክኖሎጂዎች “የግሉባላይዜሽንን” ሥርዓት እያፋጠኑት ሲሆን ኢትዬጵያም የነዚህ ቴክኖሉጂ ተጠቃሚ ከሆነች ሰነባብታለች ፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት በትምህርት ላይ እየወሰደዉ ያለዉ እርምጃ የሚያበረታታ ሲሆን ዜጎቻችን የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ያለዉ ጥረትም አንድ ማስረጃ ነዉ፡፡

ምንም እንኳ የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመንግሥትና በአንዳንድ አካሎች ጥረት ለዉጥ እያሳየ ቢሆንም፣ ህብረተሰቡን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የህብረተሰቡን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሉጂ አጠቃቀም ዕዉቅትና ክህሎት ማሳደግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ አብዛኛዉ የአገራችን ህዝብ በዝቅተኛ ገቢ የሚኖር ነዉ፡፡ ከዚህም የተነሣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖርም አገልግሎቱን ለማግኘት የቻሉትና ተጠቃሚ የሆኑት ጥቂቶች ናቸዉ፡፡ ለዚህም ዋነኛዉ ምክንያት

  • የቴክኖሎጂዉ አጠቃቀም እዉቀት ማነስ
  • የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ማነስ ሊጠቀሱ ይችላል

“ሳይበር ካፌዎችና” በዝቅተኛ ክፍያ ስልጠና የሚሠጡ ድርጅቶች አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም፡፡

ሰን ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የኮምፒውተር ማሠልጠኛ ይህን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ የሚኖረዉን ህብረተሠብ የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ በአገራችን እየተከስተ ያለዉን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት በሚያደርገዉ ጥረት የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት የተቋቋመ ማሰልጠኛ እና የትግበራ ማዕከል ነው፡፡

 our services detail  Visit our Site link !!!    https://www.suncomputeret.com